ይህ ገጽ የአማርኛን ቃላት ልማት በተግባር ለማራመድ ባለሙያዎች በየእውቀት ዘርፎቻቸው በአማርኛ ሙያዊ ቃላትን በመፍጠር፣ እንዲሁም የተፈጠሩትን በማረምና በማሻሻል ዘላቂ የአማርኛ ቃላት ማህደር ለመገንባት የሚተጋገዙበት መድረክ ነው። እንዲሁም በማናቸውም የእውቀትና የአስተሳሰብ ዘርፎች የአማርኛን ቃላትና በአጠቃላይ የቋንቋውን የፈጠራ አቅም ለማዳበር እንዲረዱ የድረገጹ ጎብኚዎች ራሳቸው የፈጠሯቸውን ወይም ለሃሳብ መግለጫነት ያስማሟቸውን ቃላት ከበቂ ማብራሪያ ጋር በዚህ መድረክ እንዲያዋጡ ይጋበዛሉ። በዚህ መድረክ ለመሳተፍም ሆነ በገጹ የሚቀርቡትን ይዘቶች ለመመልከት መጀመሪያ መመዝገብ፣ እንዲሁም ሲገቡ መለያዎችዎን ማስገባት ይጠበቅብዎታል። ማናቸውም የጎብኚዎች መለያዎች በድረገጹ አዘጋጆች በኩል ለሶስተኛ ወገን ተላልፈው አይሰጡም።